በኢዜማ ስም እና ምስል የተከፈተ ሃሰተኛ የፌስቡክ አካውንት!

ይህ ‘ኢዜማ –EZEMA’ በሚል ስያሜ በጥር ወር 2013 ዓ.ም የተከፈተና ከ1,000 በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ አካውንት የሚያጋራቸው መልዕክቶች በተለይ የኮንሶ አካባቢ ተወላጆች በሚያዘወትሯቸው የፌስቡክ ቡድኖች በስፋት ሲጋሩ ኢትዮጵያ ቼክ ተመልክቷል።

በዚህ አካውንት የተለጠፉ መልዕክቶች በተደጋጋሚ ከተጋሩባቸው የፌስቡክ ቡድኖች መካከል ከ4,500 በላይ አባት ያሉት ‘Konso Zone – ኮንሲታ ዞን’ እና ከ1,00 በላይ አባላት ያሉት ‘በኮንሶ ዞን የኢዜማ ደጋፊዎች ገጽ’ የተባሉ የፌስቡክ ቡድኖች ይገኙበታል።

በርከት ያሉ የፌስቡክ ቡድኖቹ አባላትም ገጹ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ የፌስቡክ ገጽ ስለመሆኑ ጥያቄ ሲያነሱ ኢትዮጵያ ቼክ አስተውሏል።

ገጹ የኢዜማ አለመሆኑን ኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጧል። ትክክለኛው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ ገጽ ከ109 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት እና የፌስቡክ የትክክለኛነት ማረጋገጫ ሰማያዊ ምልክት ያለበት ነው።

ተመሳስለው የተከፈቱ ሀሰተኛ ገጾችን እና አካውንቶችን ባለመከተል ከሀሰተኛና ከተዛቡ መረጃዎችን ስርጭት እራስዎን ይጠብቁ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::