የአማራ ባንክን ስምና የንግድ ምልክት

በመጠቀም የተከፈቱ ሀሰተኛ አካውንቶች፣ ገፆች እና ቻናሎች!

የአማራ ባንክን ስምና የንግድ ምልክት በመጠቀም የተከፈቱ በርከት ያሉ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች፣ ቻናሎች እና አካውንቶች ባንኩ የተለያዩ ሽልማቶችን የሚያስገኙ የውድድር መርሐ ግብሮችን እያካሄደ እንደሚገኝና የተሳተፉ ግለሰቦችም ሽልማት እንደሚያገኙ አስመስለው መረጃ ሲያጋሩ ተመልክተናል።

ሽልማት የሚያስገኙ ውድድሮች ተብለው በስፋት ከተጋሩ መካከል የመኖሪያ ቤት የሚያሸልም የሚል መልዕክት ይጠቀሳል። የኢትዮጵያ ቼክ ተከታታዮችም ስለመረጃዎቹና ስለገጾቹ ትክክለኛነት አጣርተን እንድናሳውቃቸው በተደጋጋሚ ጠይቀውናል።

ኢትዮጵያ ቼክ ጉዳዩን በተመለከተ አማራ ባንክን አነጋግሯል። የባንኩ የማርኬቲንግ ክፍል “ባንካችን ምንም አይነት ሽልማት የሚያስገኙም ሆነ ሌሎች ስጦታዎችን ያካተቱ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ዘመቻ እያስኬደ እንዳልሆነ እና ምንም አይነት መሰል የውድድር መርሐ ግብር አለማዘጋጀቱን በአጽኖት ለመግለጽ እንወዳለን” የሚል ምላሽ ሰጥቷል። ባንኩ በተጨማሪም በእንዲህ ያሉ የማጭበርበር ድርጊቶች ሃላፊነት እንደማይወስድ ገልጿል።

የአማራ ባንክ ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቹ የሚከተሉት መሆናቸውንም ለኢትዮጵያ ቼክ አሳውቋል።

ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/amharabanksc1

ቴሌግራም:- https://t.me/Amhara_Banksc

ትዊተር:- https://twitter.com/Amharabanksc

ተመሳስለው የሚከፈቱ ገፆችን፣ አካውንቶችን እና ቻናሎችን ባለመከተል ራሳችንን ከሀሰተኛ መረጃ እና የጥላቻ ንግግሮች እንጠብቅ የዘወትር መልዕክታችን ነው።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::