በቴሌብር ስም እና ንግድ ምልክት ተመሳስለው የተከፈቱ ገፆችና አካውንቶች! 

ኢትዮ ቴሌኮም ዛሬ ለደንበኞቹ ባሰራጨው አጭር የጽሁፍ መልዕክት የቴሌብር ስምን እና ንግድ ምልክትን በመጠቀም ተመሳስለው የተከፈቱ ሀሠተኛ የፌስቡክና የቴሌግራም አካውንቶች መኖራቸውን አስታውቋል። 

ድርጅቱ እንደገለጸው በነዚህ ሀሠተኛ አካውንቶች የቴሌብር አገልግሎትን በተመለከተ የተሳሳተ መረጃ ሊሰራጭ ስለሚችል ደንበኞች የቴሌብርን ትክክለኛ የፌስቡክና የቴሌግራም አካውንቶችን እንዲከተሉ መክሯል። 

ኢትዮጵያ ቼክም ባደረገው ምልከታ የቴሌብርን ስምና የንግድ ምልክት በመጠቀም የተከፈቱ በርካታ የፌስቡክና የቴሌግራም አካውንቶች መኖራቸውን አረጋግጧል። 

የቴሌብር ትክክለኛ አካውንቶችን ከታች የተያያዙትን ማስፈንጠሪያዎች በመከተል ማግኘት ይቻላል። 

ፌስቡክ:-  https://www.facebook.com/telebirr 

ቴሌግራም:-  https://t.me/telebirr 

ኢትዮ ቴሌኮም ከሳምንታት በፊት ቴሌብር የተሰኘ የሞባይል ገንዘብ ማስተላለፊያና የመገበያያ ዘዴ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::