የጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይን ስምና ፎቶ በመጠቀም ከተከፈተ ሀሰተኛ የፌስቡክ ገጽ እንጠንቀቅ!

የካቲት 13፣2015

የጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይን ስምና ፎቶ በመጠቀም በትናንትናው ዕለት የተከፈተ የፌስቡክ ገጽ መኖሩን ተመልክተናል።
ይህ ገጽ የጋዜጠኛው የቀድሞው አካውንቱ እንደተዘጋና አዲስ ለመክፈት መገደዱን በመግለጽ ሰዎች እንዲከተሉት ሲገፋፋም አስተውለናል። በዚህም በአሁኑ ሰዐት ከ1,700 በላይ ተከታዮችን ማግኘት ችሏል።
በተጨማሪም የቴሌግራም አካውንት እንዳለው በመግለጽ ወደ አካውንቱ የሚያመራ ማስፈንጠሪያ (link) አያይዟል።
ሆኖም ከላይ የተጠቀሰው የፌስቡክ ገጽ ሀሰተኛ መሆኑን ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ለኢትዮጵያ ቼክ አሳውቋል።
የጋዜጠኛ ጎበዜ ትክክለኛ የፌስቡክ ገጽ ከ83 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ሲሆን ይህን ማስፈንጠሪያ በመከተል ማግኘት ይቻላል:
ተመሳስለዉ የተከፈቱ የማህበራዊ ትስስር ገጾች እና አካዉንቶች ለሀሰተኛ እና አሳሳች መረጃዎች ሊያጋልጡን ስለሚችሉ ጥንቃቄ እናድርግ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::