“ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ ሙሃመድ የትዊተር አካዉንት የላቸዉም”— የሶማሌ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለኢትዮጵያ ቼክ

የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ ሙሃመድን ስም እና ምስል በመጠቀም የተከፈቱ የትዊተር አካዉንቶች የተለያዩ መልክቶችን እየለጠፉ ይገኛሉ።

በተለይ ከ4,000 በላይ ተከታዮች ያሉት አካዉንት በትላንትናዉ ዕለት ብቻ ከ10 በላይ መልክቶችን ለጥፏል።

ኢትዮጵያ ቼክ ይህንና መሰል የትዊተር አካዉንቶች እዉነተኛነት ለማረጋገጥ በሶማሌ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የመረጃ ስርጭትና ዲጂታል ሚዲያ ዳይሬክተር የሆኑትን አቶ አብዲዴቅ መሀመድን አናግሯል።

እርሳቸዉም ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ ሙሃመድ አሁን ላይ የትዊተር አካዉንት እንደሌላቸዉ ነግረዉናል። በሌላ በኩል ፕሬዝዳንቱ የተረጋገጠ የፌስቡክ አካዉንት እንዳላቸዉም ነግረዉናል (https://www.facebook.com/mustafa.omer.146)።

ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችንና ገጾችን ብቻ በመከተል እራስዎን ከተዛቡ እና ሀሠተኛ ከሆኑ መረጃዎች ያርቁ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::