በአርቲስት ታሪኩ ጋንኪሲ ስም እና ፎቶ ተመሳስለው የተከፈቱ ሀሰተኛ የፌስቡክ አካውንቶች!

“ድሽታ ግና” በሚል ተወዳጅ ስራው እውቅና ያገኘው አርቲስት ታሪኩ ጋንኪሲ ስሙን እና ፎቶውን በመጠቀም በርካታ የፌስቡክ አካውንቶች እንደተከፈቱ ተመልክተናል። ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ቅኝት ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው ሰባት አካውንቶች በስሙ ተከፍተው ይገኛሉ።

በተለይ በትናንትናው እለት በምስሉ ላይ የሚታየውን ፅሁፍ አርቲስቱ እንደፃፈ ተደርጎ በአንድ የሀሰተኛ አካውንት አማካኝነት የቀረበ ሲሆን ይህም በከፍተኛ ደረጃ በተለይ ፌስቡክ ላይ ተሰራጭቷል።

ግንቦት ወር ላይ አርቲስቱ ለኢትዮጵያ ቼክ ትክክለኛው አካውንቱ ይህ እንደሆነ አስታውቆ ነበር: https://www.facebook.com/tariku.gankise

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::