በአርቲስት መሰረት መብራቴ ስም እና ምስል ተመሳስሎ የተከፈተ የትዊተር አካውንት!

የዛሬ ሁለት ወር ገደማ በአርቲስት መሰረት መብራቴ ስም እና ምስል ተመሳስሎ የተከፈተ የትዊተር አካውንት እንዳለ ተመልክተናል።

አካውንቱ በርካታ መልእክቶችን እያስተላለፈ የሚገኝ ሲሆን በሁለት ወር ውስጥ ብቻ ከ3,600 በላይ ተከታይ ማፍራት ችሏል፣ አካውንቱ ላይ የሚቀርቡት መልእክቶችም በርካታ ግብረ-መልሶችን እያገኙ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ አካውንት ዙርያ አርቲስት መሰረትን ያናገረ ሲሆን የእርሷ እንዳልሆነ አረጋግጣለች።

በአርቲስቷ ስም የተከፈቱ በርካታ የፌስቡክ ገፆችም ይገኛሉ። አርቲስት መሰረት የምትጠቀምባቸው ትክክለኛ የፌስቡክ አካውንት እና ገፅ የሚከተሉት ናቸው:

የፌስቡክ አካውንት: https://www.facebook.com/officialmesertmebrate/

የፌስቡክ ገፅ: https://www.facebook.com/meseret.mebratie.1

ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችንና ገጾችን በመከተል እራስዎን ከተዛቡ እና ሀሠተኛ ከሆኑ መረጃዎች ያርቁ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::