በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ስም የተከፈቱ ሀሠተኛ የፌስቡክና የትዊተር ገጾች!

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ስም ተከፍተው የነበሩ ሀሠተኛ የፌስቡክና የትዊተር ገጾችን ለተከታታዮቻችን ማሳወቃችን ይታወሳል።

የዶክተር ይልቃል ከፋለ ትክክለኛ የፌስቡክና የትዊተር አካውንቶችን እንድጠቁማቸውም በርካቶች ጥያቄ አቅርበውልን ነበር።

የዶክተር ይልቃል ከፋለ አዲስ የተከፈቱ እና ትክክለኛ የፌስቡክና የትዊተር አካውንቶች የሚከተኩት መሆናቸውን የክልሉ መንግስት ለኢትዮጵያ ቼክ አስታውቋል።

ትክክለኛዎቹን አካውንቶች ለማግኘት ማስፈንጠሪያዎችን ይከተሉ

ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/103775735412694/posts/126006503189617/
ትዊተር:- https://twitter.com/AserseKefale?t=vEQMH8W4Et9Cm3iHCdXi3g&s=09

ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችንና ገጾችን ብቻ በመከተል እራስዎን ከተዛቡ እና ሀሠተኛ ከሆኑ መረጃዎች ያርቁ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::