በከተማና መሰረተ-ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ ስም እና ምስል የተከፈተ ሀሰተኛ የትዊተር አካውንት!

አሁን አሁን የታዋቂ ግለሰቦችን፣ ፖለቲከኞችን፣ ሚድያዎችን እንዲሁም ተቋማትን ስም እና ምስል በመጠቀም ማህበራዊ ሚድያ ላይ አካውንት፣ ገፅ እንዲሁም ቻናሎችን መክፈት እየተበራከተ መጥቷል።

የዚህ ድርጊት አንዱና ዋነኛ አላማ በነዚህ ግለሰቦች እና አካላት ስም ሀሰተኛ መረጃዎችን ጨምሮ የተለያዩ ፅሁፎችን፣ ምስሎችን እና ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማሰራጨት ነው። ድርጊቱ ደግሞ በማህበራዊ ሚድያ ተቋማት ዘንድም ሆነ በመላው ማህበረሰብ በኩል ተቀባይነት የለውም።

ኢትዮጵያ ቼክ በተከታታይ ከሚያቀርባቸው መረጃዎች መሀል እነዚህን ሀሰተኛ ገፆች ለተከታታዮቹ መጠቆም ይገኝበታል፣ ወደፊትም ይቀጥላል።

ለዛሬ በከተማና መሰረተ-ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ ስም እና ምስል ስለተከፈተ ሀሰተኛ የትዊተር አካውንት አንድ እንበላችሁ።

ሀሰተኛ ገፁ የተከፈተው የዛሬ አራት ወር ገደማ ሲሆን አሁን ላይ ከ4,400 በላይ ተከታይ አለው፣ በርካታ ስሜት ቆስቋሽ ፅሁፎችን ስለሚያቀርብ ብዙ ግብረ-መልስ (ኮመንት፣ ሼር እና ሪትዊት) ያገኛል።

ትክክለኛው የሚኒስትሯ የትዊተር አካውንት ደግሞ ከቀናት በፊት የተከፈተ ሲሆን አሁን ላይ 600 ገደማ ተከታዮች አሉት (link: https://twitter.com/chaltuofficial?t=Q2ffz1T9HSQgQh9aO2yeuA&s=09)። ይህም በግልፅ እንደሚያስረዳው አንዳንድ ግዜ የአንድን ገፅ ትክክለኛነት ለማወቅ የተከታይ ሰው ብዛት እንደማይጠቅም ነው።
ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችንና ገጾችን በመከተል እራስዎን ከተዛቡ እና ሀሠተኛ ከሆኑ መረጃዎች ያርቁ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::