የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ አወል አርባን ስምንና ምስል በመጠቀም የተከፈተ የፌስቡክ ገጽ መኖሩን ተመልክተናል!

ይህ “Awol Arbaa Undie – አወል አርባ ኡንዴ” የሚል መጠሪያ ያለው የፌስቡክ ገጽ እ.አ.አ ጥቅምት 12/2021 ዓ.ም የተከፈተ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከ15 ሺህ በላይ ተከታዮች አሉት።

ገጹ የተከፈተ ሰሞን የርዕሰ መስተዳደሩን ፎቶዎች ያጋራ የነበረ ሲሆን ቆየት ብሎ ጽሁፎችን መለጠፍ መጀመሩን አስተውለናል። በዚህም በሺህዎች የሚቆጠር ግብረመልሶችን እንደሚያገኝ ተመልክተናል።

ኢትዮጵያ ቼክ የአካውንቱን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የአፋር ክልል የመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮን አነጋግሯል። የቢሮው ሃላፊ አቶ አህመድ ካልዮታ ከላይ የተጠቀሰው ገጽ ሀሠተኛ መሆኑን የገለጹ ሲሆን አቶ አወል አርባ ምንም አይነት የፌስቡክ አካውንትም ሆነ ገጽ እንደሌላቸው አሳውቀዋል።

ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችንና ገጾችን ብቻ በመከተል እራሳችንን ከተዛቡ እና ሀሠተኛ ከሆኑ መረጃዎች እናርቅ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::