የአርቲስት አቡሽ ዘለቀን ስምና ምስል በመጠቀም የተከፈቱ ሁለት የትዊተር አካውንቶች መኖራቸውን ተመልክተናል!

አንደኛው አካውንት በነሀሴ ወር 2013 ዓ.ም የተከፈተ ሲሆን ከ4,440 በላይ ተከታዮችን ማፍራት ችሏል። ሌላኛው አካውንት በታህሳስ ወር 2014 ዓ.ም የተከፈተ ሲሆን ከ11,800 በላይ ተከታዮች አሉት።

ኢትዮጵያ ቼክ የትዊተር አካውንቶቹን ትክክለኛነት ለማጣራት አርቲስት አቡሽን ያነጋገረ ሲሆን ከላይ የተጠቀሱት ሁለት የትዊተር አካውንቶች የእርሱ አለመሆናቸውን አረጋግጧል።

በአርቲስቱ ስም የተከፈቱ የፌስቡክ ገፆችም ይገኛሉ። ከወራት በፊት ወደ 100 ሺህ ገደማ ተከታይ የነበረው አንድ ሀሰተኛ አካውንትን ፌስቡክ ዘግቷል። አርቲስት አቡሽ የሚጠቀምበት ትክክለኛ የፌስቡክ አካውንት የሚከተለው ነው: https://m.facebook.com/Abbush.Zallaqaa

ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችንና ገጾችን ብቻ በመከተል እራሳችንን ከተዛቡ እና ሀሠተኛ ከሆኑ መረጃዎች እናርቅ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::