“ለመንግስት ያስገባሁት የመልቀቂያ ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷል፣ በጤና እክል ምክንያት ቀደም ብዬ ጡረታ ወጥቻለሁ፣ “— የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም ለኢትዮጵያ ቼክ

የኢትዮጵያ አየር መንገድን ከ37 አመት በላይ በተለያዩ የስራ ዘርፎች ያገለገሉት አቶ ተወልደ ገ/ማርያም በጤና እክል ምክንያት ቀደም ብለው ጡረታ መውጣታቸውን ለኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጠዋል። አክለውም ለመንግስት ያስገቡት የመልቀቂያ ጥያቄም ተቀባይነት ማግኘቱን አሳውቀውናል።

አቶ ተወልደ ላለፉት 11 አመታት በዋና ስራ አስፈፃሚነት ያገለገሉ ሲሆን ከዛ በፊት በካርጎ ክፍል ሀላፊነት፣ በአሜሪካ ኤሪያ ማናጀር በመሆን ወዘተ ሰርተዋል። በዚህም ወቅት “የአመቱ ምርጥ የአፍሪካ ስራ አስፈፃሚ” የሚሉ ሽልማቶችን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ሽልማቶችን ለግላቸውም፣ ለአየር መንገዱም አስገኝተዋል።

የአየር መንገዱ አዲስ ስራ አስፈፃሚ ማን እንደሚሆን እስካሁን ይፋ አልተደረገም።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::