ኢትዮጵያ፣ የአፍሪካ

አንድነት ድርጅት እና የሊግ ኦፍ ኔሽን ምስረታ!

ዛሬ (ሰኔ 30 2014) ፓርላማው በነበረው ውሎ ላይ ከተነሱት ጉዳዮች መሀል ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አንድነት ድርጅት (አሁን አፍሪካ ህብረት) እንዲሁም ሊግ ኦፍ ኔሽን በመባል ይታወቅ በነበረው ድርጅት ዙርያ የነበራት ተሳትፎ ነበር። 

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ኢትዮጵያ ለአለም የነበራትን እና አሁን ላይ ያላትን አስተዋፆ በተመለከተ ባደረጉት ንግግር ላይአፍሪካን ዩንየን ከመሰረቱ ሶስት ሀገራት ኢትዮጵያ አንዷ ነችብለዋል። ይሁን እንጂ ያሁኑ የአፍሪካ ህብረት (የቀድሞዉ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት) ..አ ግንቦት 1963 ሲመሰረት የምስረታ ቻርተሩን የፈረሙት 32 የአፍሪካ ሀገራት መሆናቸውን የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ (ማጣቀሻ: የአፍሪካ ህብረት ድረገፅ: https://au.int/en/overview) 

በሌላ በኩል ፓርላማ በቀረበው ንግግር ላይሊግ ኦፍ ኔሽንን ከአፍሪካ ብቸኛዋ መስራች ሀገር ኢትዮጵያ ናትየሚል መረጃ ቀርቧል። ኢትዮጵያ ይህን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቀደም ብሎ የነበረ ተቋም ቀድመው ከተቀላቀሉ ጥቂት የአለም ሀገራት አንዷ ነበረች፣ ነገር ግን የዚህ ሊግ ኦፍ ኔሽን የተባለ ቅኝ ገዢ ሀገራት በበላይነት የተቆጣጠሩት ድርጅት ምስረታ ላይ ተሳትፎ አልነበራትም። ሊግ ኦፍ ኔሽን እ..አ በ1920 የተቋቋመ ሲሆን ኢትዮጵያ ደግሞ ሊጉን የተቀላቀለችው ከሶስት አመት በኋላ እ..አ በ1923 (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር መስከረም 17 ቀን 1916 /) ነበር (ማጣቀሻ: አዲስ ዘመን ጋዜጣ: https://www.press.et/?p=62450)

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::