የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ስምና አርማ በመጠቀም የተከፈተ የትዊተር አካውንት

ነሐሴ 27 2014

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ስምና አርማ በመጠቀም የተከፈተ የትዊተር አካውንት መኖሩን ተመልክተናል። 

ይህ ‘Ethiopian Orthodox Tewahedo Church’ የሚል ስያሜ ያለው አካውንት አሁን ላይ 2,108 ተከታዮች አሉት። አካውንቱ እራሱን የቤተክርስቲያኒቱ ኦፊሴላዊ (official) የትዊተር አካውንት እንደሆነ የሚገልጽ ሲሆን ከቤተክርስቲያኒቱ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን እንደሚያጋራ አስተውለናል። 

ኢትዮጵያ ቼክ የአካውንቱን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን አነጋግሯል። 

የቤተክርስቲያኒቱ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ከላይ የተገለጸው የትዊተር አካውንት የቤተክርስቲያኗ አለመሆኑን ገልጿል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ሃላፊ ሊቀ ስዩማን እስክንድር ገ/ክርስቶስ በአካውንቱ የሚጋሩ መልዕክቶችም ቤተክርስቲያኒቱን እንደማይወክሉ ለኢትዮጵያ ቼክ አሳውቀዋል። 

ተመሳስለው የተከፈቱ ሀሰተኛ ገጾችን እና አካውንቶችን ባለመከተል ከሀሰተኛና ከተዛቡ መረጃዎችን ስርጭት እራሳችንን እንጠብቅ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::