የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት “አምባሳደር ተሾመ ቶጋ በሚወዳደሩበት ወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ መራጩ  ድምጻቸውን በመስጠት ላይ ናቸው” የሚል መረጃ በፌስቡክ ገጹ ለጥፏል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አምባሳደር ተሾመ ይወዳደሩበታል ብሎ የጠቀሰው ቦታ የተሳሳተ ነው። 

ኢትዮጵያ ቼክ መረጃውን ለማጣራት  የዕጩዎች ዝርዝርንና የሚወዳደሩበትን  ቦታ ከምርጫ ቦርድ ድረ-ገጽ የተመለከተ ሲሆን አምባሳደር ተሾመ በወላይታ ዞን ሶዶ  ከተማ ሳይሆን በዳሞት ወይዴ—2 የምርጫ ክልል እንደሚወዳደሩ አረጋግጧል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::