የዶክተር ዳኛቸው አሰፋን ስምና ምስል በመጠቀም የተከፈቱ የትዊተር አካውንቶች

መስከረም 09፣ 2015

የዶክተር ዳኛቸው አሰፋን ስምና ምስል በመጠቀም የተከፈቱ የትዊተር አካውንቶች መኖራቸውን ተመልክተናል። ከአካውንቶች መካከል አንደኛው እ.አ.አ ሚያዚያ 2014 ዓ.ም የተከፈተ ሲሆን 5,338 ተከታዮች አሉት።

ሌላኛው ከሳምንታት በፊት የተከፈተ ሲሆን ከ1,900 በላይ ተከታዮችን ማፍራት ችሏል። ይህ ‘Dr. Dagnachew Assefa of AAU’ የሚል ስያሜን የሚጠቀመው የትዊተር አካውንት በሚያጋራቸው መልዕክቶች በመቶዎች የሚቆጠሩ ግብረመልሶችን እንደሚያገኝም አስተውለናል።

ኢትዮጵያ ቼክ አካውንቶቹን በተመለከተ ዶክተር ዳኛቸውን አነጋግሯል። ዶክተር ዳኛቸው ትዊተር ተጠቅመው እንደማያውቁ ገልጸው ከላይ የተገለጹት አካውንቶችም ሆነ በአካውንቶቹ የሚጋሩት መልዕክቶች የእርሳቸው አለመሆናቸውን አሳውቀዋል።

ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ የፍልስፍና መምህር ሲሆኑ በጋዜጣ፣ በሬዲዮ፣ በቴሌቪዝን እንዲሁም በአደባባይ ሀሳባቸውን በመግለጽ ይበልጥ ይታወቃሉ።

ተመሳስለው የተከፈቱ ሀሰተኛ ገጾችን እና አካውንቶችን ባለመከተል ከሀሰተኛና ከተዛቡ መረጃዎችን ስርጭት እራሳችንን እንጠብቅ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::