ይህ ምስል በላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያን ላይ የደረሰ ጉዳትን ያሳያል?

ከሰሞኑ በርካቶች ይህን ምስል በመጠቀም በላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያን ላይ ጉዳት እንደደረሰ ማህበራዊ ሚድያ ላይ ፅፈዋል፣ የኢትዮጵያ ቼክ ተከታታዮችም ይህን እንድናጣራ ጥያቄ ልከውልናል። 

የሞባይል መተግበርያዎችን በመጠቀም ባደረግነው ማጣራት ምስሉ ላይ የሚታየው ክፍተት ድሮም የነበረ እና የሚታየው ፎቶ ደግሞ እ.አ.አ በኦገስት 15/2019 ኢንተርኔት ላይ የተለቀቀ መሆኑን አይተናል (ሊንክ: https://fineartamerica.com/featured/2-biete-amanuel-underground-orthodox-monolith-lalibela-ethiopia-artush-foto.html?product=puzzle) 

ከዚህም በተጨማሪ ነጠብጣቦቹ ምን እንደሆኑ በከርቲን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ይርጋ ገላው የፃፉትን ተመልክተናል። ዶ/ር ይርጋ ይህን ሲያስረዱ “The holes in the surface were caused by the insertion and removal of nails” በማለት ነጠብጣቦቹ/ቀዳዳዎቹ ቦታው ላይ ሚስማር በማስገባት እና በማስወጣት የተከሰተ እንደሆነ አስረድተዋል (ሊንክ: https://www.researchgate.net/figure/Bete-Amanuel-the-tortured-church-The-holes-in-the-surface-were-caused-by-the-insertion_fig3_329584472) 

ከሀሰተኛ መረጃዎች ጋር የሚቀርቡ እንዲህ ያሉ ምስሎችን ባለማጋራት ሀላፊነትዎን ይወጡ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::