የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የፓርቲዎች እጩዎችን በሀይማኖት ለይቶ ይመዘግባል? 

የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በመጪው ሀገራዊ ምርጫ የሚሳተፉ እጩዎችን በሀይማኖት ለይቶ እንደመዘገበ የሚጠቁሙ መረጃዎች በተለይ ማህበራዊ ሚድያ ላይ እየተፃፈ ይገኛል፣ አንዳንዶችም የእጩዎችን የሀይማኖት ስብጥር ዝርዝር ያሳያል ያሉትን መረጃ ከምርጫ ቦርድ እንዳገኙ በመጥቀስ መረጃ እያጋሩ ይገኛሉ። 

ኢትዮጵያ ቼክ የመረጃውን ትክክለኛነት ለማጣራት የቦርዱን የኮሚኒኬሽን ሀላፊ ሶልያና ሽመልስን እናግሯል። 

ሀላፊዋ እንደነገሩን ቦርዱ ሲጀምር በጠቅላላ ዘጠኝ ሺህ የሚሆኑትን የእጩዎች ዝርዝር መረጃን እስካሁን ይፋ አላረገም። ሌላው እና ዋናው ነገር ደግሞ ቦርዱ የሚሰበስበው የእጩዎች ዝርዝር ላይ ምንም አይነት የሀይማኖት ስብጥርን አያሳይም። 

“እኛ የእጩዎችን ሀይማኖት የሚጠይቅ ዶክመንት አንጠይቅም፣ ስለዚህ ይህ ከምርጫ ቦርድ ተገኘ ተብሎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ የሀሰት ነው” ብለው ለኢትዮጵያ ቼክ ተናግረዋል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::