“ጀግኒት ተሸለመች” በሚል ርዕስ የተጋራዉ የኮ/ር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ምስል በቅንብር የቀረበ ነዉ!

የዲጂታል ሚድያዎችን፣ የመንግስት ቢሮዎችን እና አንዳንድ ጋዜጠኞችን ጨምሮ “ጀግኒት ተሸለመች” በሚል ርዕስ “አትሌት ኮ/ል ደራርቱ ቱሉ ላደረገችው አስተዋፅኦ ከአለም ኦሎምፒክ ኮሚቴ እጅግ ዘመናዊ BMW መኪና ተሸለመች” የሚል ፅሁፍ ማህበራዊ ሚድያ ላይ በስፋት ሲሰራጭ ተመልክተናል።

ኢትዮጵያ ቼክ በምስሉ ላይ ባደረገው ማጣራት መኪናው “Iran BMW Strathan” በተባለ የትዊተር አካውንት ላይ እ.አ.አ ጁላይ 9, 2022 ተጋርቶ የነበረ ምስል እንደሆነ አረጋግጧል። እዚህ ምስል ላይ የኮ/ር አትሌት ደራርቱ ቱሉን ምስል በቅንብር በማስገባት የቀረበ እንደሆነ ማየት ችለናል።

ከተሳኩ የስፖርታዊ ውድድሮች በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገራት ለስፖርተኞች እና የስፖርት አመራሮች ሽልማቶችን መስጠት የተለመደ ነው።

በአሜሪካ፣ ኦሬገን በተካሔደው የአትሌቲክስ ውድድር ከአለም ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ ቡድን ነገ ምሽት ወደሀገር ከተመለሰ በሗላ ሽልማት እንደሚበረከትለት ኢትዮጵያ ቼክ ያገኘው መረጃ ይጠቁማል።

ነገር ግን በማህበራዊ ሚድያ የተሰራጨው ይህ መረጃ ሀሰተኛ እንደሆነ ማረጋገጥ ችለናል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::