የሩስያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ዛሬ በኢትዮጵያ ዙርያ መግለጫ ሰጥተዋል?

ጄዚራ አፍሪካ Jazeera Africa” የተባለ ከ136,000 በላይ ተከታይ ያለው የፌስቡክ ገፅ የሩስያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ዛሬ በኢትዮጵያ ዙርያ መግለጫ እንደሰጡ አድርጎ መረጃ አውጥቷል። 

በፅሁፉም “ፕሬዘዳንት ብላድሚር ፑቲን መገለጫ, the statement of President pladmir putin” የሚል ሲሆን ፕሬዝደንቱ ተናገሩ ያላቸውን በርካታ ነጥቦች አንስቷል፣ እኛም ከተከታታዮቻችን እንድናጣራ ጥያቄ ቀርቦልናል። 

አዲስ አበባ ከሚገኘው የሩስያ ኤምባሲ ያገኘው አጭር መረጃ “መረጃውን ስላደረሳችሁን እናመሰግናለን፣ ይህ መረጃ ፍፁም ውሸት ነው” ይላል። ገፁ ሌሎች ያልተረጋገጡ እና ሀሰተኛ መረጃዎችን እያሰራጨ እንደሚገኝ ተመልክተናል፣ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እንመክራለን።

Update: የተመድ የአለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አውሮፕላኑ በድርጅቱ ስር የሚተዳደር እንደነበር ገልፆ በረራው ከድሬዳዋ ወደ ጅግጅጋ እንደነበር ጠቅሷል። አክሎም ሁለቱ ተሳፋሪዎች የድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን (MSF) ሰራተኞች፣ ሁለቱ ደግሞ የበረራ ባለሙያዎች እንደሆኑ ጠቅሶ ከአደጋው በሗላ ወደ ድሬዳዋ ለህክምና ምርመራ እንደተወሰዱ አሳውቋል፣ የአደጋው መንስኤም ይጣራል ብሏል። 

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::