የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳደሪ አቶ ባይነሳኝ ዘሪሁን ታስረዋል?

“የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳደሪ አቶ ባይነሳኝ ዘሪሁን ታስረዋል እየተባለ የሚናፈሰው አሉባልታውሸት ነው“— የአዊ ዞን ኮሚኒኬሽን
በተለያዩ ግለሰቦችና ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ዋና አስተዳዳሪው ታስረዋል ተብሎ የሚናፈሰው አሉባልታ“ከዕውነት የራቀና ፍፁም ውሸት” ብሎ የዞኑ ኮሚኒኬሽን መረጃ አጋርቷል።
ኮሚኒኬሽኑ “አስተዳዳሪው አሁንም በመደበኛ የመንግስት ስራ ላይ ያሉ እና ባለጉዳዮቻቸውን በተለመደውአግባብ እያስተናገዱ ያሉ ናቸው” ብሎ መረጃ ያጋራ ሲሆን “በዚህ ምንም ፋይዳ በሌለው አጀንዳ ላይ የሆናችሁአካላት አካሄዱ ለህዝብም፣ ለሀገርም ፋይዳ የሌለው መሆኑን ተረድታችሁ ከዚህ ተግባር እንድትታቀቡና ህዝብከማደናገር እኩይ ተግባር ብትወጡ መልካም ነው” ብሏል።
ኢትዮጵያ ቼክ በስፍራው ካሉ ምንጮች ማጣራት የቻለው መረጃው የተሳሳተ መሆኑን እና አስተዳዳሪው ስራ ላይመሆናቸውን ነው።
ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ
ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::