አትሌት ዋሚ ቢራቱ ሞተ ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ውሸት ነው!

አባቴ አትሌት ዋሚ ቢራቱ ሞተ ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ውሸት ነው፣ እንዲህ አይነት ስራ በሚሰሩ ሰዎችበጣም አዝናለሁ“— ጃገማ ዋሚ ቢራቱ ለኢትዮጵያ ቼክ

በርካታ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ማምሻውን አንጋፋው አትሌት ዋሚ ቢራቱ እንዳረፉ መረጃአሰራጭተዋል፣ 1.5 ሚልዮን በላይ ተከታዮች ያሉት ሀበሻም ይህን መረጃ ካጋራ በሗላ ከገፁ ላይ አጥፍቷል።

ኢትዮጵያ ቼክ ከአትሌት ዋሚ ቢራቱ ልጅ ጃገማ ዋሚ ቢራቱ ማረጋገጥ የቻለው መረጃው የውሸት መሆኑን ነው።

አባቴ አትሌት ዋሚ ቢራቱ ሞተ ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ውሸት ነው፣ እንዲህ አይነት ስራ በሚሰሩ ሰዎችበጣም አዝናለሁብሎ ለኢትዮጵያ ቼክ መረጃ የሰጠው ጃገማአባቴ በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛል፣ ዛሬ ጠዋትራሱ በስልክ አውርተናልብሏል።

ኢትዮጵያ ቼክ ያናገራት / አትሌት ደራርቱ ቱሉምውሸት ነው፣ ከቤተሰብም ሆነ ከጓደኞች አረጋግጫለሁብላለች።

በሀሰተኛ መረጃ ዙርያ አስተያየት የሰጠን ጃገማህብረተሰቡ የሀሰተኛ መረጃዎች ላይ ጥንቃቄ ሊያረግ ይገባል።ይህንን የሚፅፉ ሁሉ ሀላፊነት ሊሰማቸው ይገባል። ለነገሩ እኛ እንዲህ ተብሎ እንደተወራ ለአባታችንአንነግረውም፣ ሲጀምርም እሱ ለወሬ ቦታ የለውምብሏል።

አትሌት ዋሚ 104 አመት እድሜ ባለፀጋ ሲሆኑ ሩጫን የተቀላቀሉት በውትድርና አገራቸውን እንዲያገለግሉተመድበው አስመራ በነበሩበት 1945 . እንደሆነ የታሪክ ድርሳናት ያሳያሉ።

ከዚያን ዘመን አንስቶ በተለያዩ ጊዜያት ለአገራቸው ድልን በማስመዝገብ እንደ አበበ ቢቂላ ላሉ ብርቅዬ አትሌቶችአርአያ ሆነዋል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::