40/60 3ኛ ዙር የጋራ መኖርያ ቤት እጣ ባለ እድሎች ስም ዝርዝር እስካሁን አልተለቀቀምየአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ለኢትዮጵያ ቼክ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 14ኛ ዙር 20/80 እና 3ኛዉን ዙር 40/60 የጋራ መኖርያ ቤት እጣ ማዉጣት ስነስርዓት ከሁለት ቀናት በፊት ማካሄዱ ይታወቃል። 

ይህን ተከትሎ በዛሬዉ እለት የ40/60 ባለ ሁለት እና ሶስት መኝታ ቤት ባለ እድለኞች ስም ዝርዝር የሚል ፋይል (PDF) በተለይም በፌስቡክ እንዲሁም በቴሌግራም ግሩፖችና ቻነሎች አማካኝነት ሲሰራጭ ተመልክተናል። 

በርካታ የኢትዮጵያ ቼክ ተከታዮችም መረጃዉን ትክክለኛነት እንድናጣራ ጥቆማዎችን ልካችሁልናል። 

ኢትዮጵያ ቼክ በጉዳዩ ላይ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራትን ያናገረ ሲሆንእኛ ኦፊሺያሊ አልለቀቅንምብለዋል። 

በተጨማሪምዌብሳይት ላይ እንለቃለን፤ ጋዜጣም እናትማለን ብለናል። ነገር ግን ያልተጠናቀቁ ስራዎች ስላሉ እስካሁን አልለቀቅንም። በየቦታዉ እኛም እንደናንተዉ እንሰማለን። ትክክል አይደለምሲሉ ለኢትዮጵያ ቼክ ነግረዋል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::