ከ183 ሺህ በላይ ተከታይ ያለው እና በጋዜጠኛ ቤተልሄም ታፈሰ ስም እና ምስል የተከፈተ የፌስቡክ ገፅ!

ይህ ከ183 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት እና የጋዜጠኛ ቤተልሔም ታፈሰን ስም እና ምስል በመጠቀም የተከፈተ የፌስቡክ ገጽ የእርሷ አለመሆኑን ጋዜጠኛ ቤተልሔም ለኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጣለች።

በዚህ ሀሰተኛ ገጽ በየዕለቱ በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋዎች የፖለቲካ ይዘት ያላቸው በርካታ መልዕክቶች የሚለጠፉ ሲሆን ከተከታዮቹ በሺህዎች የሚቆጠር ግብረመልስ ሲያገኝ ኢትዮጵያ ቼክ ተመልክቷል።

ገፁ በመስከረም ወር ላይ እንደተከፈተ የተመለከትን ሲሆን ሁለት ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሰዎችም በአድሚንነት ይቆጣጠሩታል። በገፁ ላይ የሚቀርቡት ፅሁፎች በጣም አነጋጋሪ፣ ሌሎቹ ደግሞ በሀሰተኛ መረጃ ላይ ተንተርሰው የሚቀርቡ ስለሆኑ በአጭር ግዜ በርካታ ተከታዮችን ለማፍራት ችሏል።

ተመሳስለው የተከፈቱ ሀሰተኛ ገጾችን እና አካውንቶችን ባለመከተል ከሀሰተኛና ከተዛቡ መረጃዎችን ስርጭት እራስዎን ይጠብቁ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::