አቶ ግርማ ዋቄ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሾሙት በቦርድ ሊቀመንበርነት እንጂ በዋና ስራ አስፈፃሚነት አይደለም።

በእንግሊዘኛ ቋንቋ የሚታተመው ሳምንታዊው ካፒታል ጋዜጣ አቶ ግርማ ዋቄ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ (CEO) እና የቦርድ ሊቀመንበር (Chairman) ሆነው መሾማቸውን የሚገልጽ መረጃ በፌስቡክና በትዊተር ገጾቹ በትናንትናው እለት አጋርቷል።

ካፒታል ጋዜጣ አቶ ግርማ ዋቄ ዋና ስራ አስፈጻሚ በመሆን ተሹመዋል በማለት ያጋራው መረጃ የተሳሳተ ሲሆን አየር መንገዱ በትናትናው ዕለት ባወጣው ኦፊሴላዊ መግለጫ እንዳስታወቀው አቶ ግርማ ዋቄ የተሾሙት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ ሠብሳቢ እና ፕሬዝደንት በመሆን ነው።

በተጨማሪም አቶ መስፍን ጣሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስራ አስፈፃሚ ሆነው መሾማቸውን ቦርዱ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል።

ሆኖም ጋዜጣው መረጃውን ካጋራ 18 ሰዐታት ቢቆጠሩም የእርምት እርምጃ አለመውሰዱን ተመልክተናል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::