በአርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ስም እና ምስል የተከፈተ ሀሰተኛ የፌስቡክ ገፅ! 

ከ240,000 በላይ ተከታይ ያለው በአርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ስም እና ምስል የተከፈተ ሀሰተኛ የፌስቡክ ገፅ የተለያዩ መልእክቶችን እያስተላለፈ ይገኛል። አርቲስቱ ይህ ገፅ የእርሱ እንዳልሆነ ለኢትዮጵያ ቼክ አሳውቋል። 

ትክክለኛው አካውንቱ ይህ እንደሆነ የገለፀ ሲሆን (https://www.facebook.com/netsanet.workneh.7) ተመሳስሎ በተከፈተው ገፅ ላይ የሚተላለፈው መልእክት የርሱ እንዳልሆነ አሳስቧል። 

ሀሰተኛ አካውንቶችን፣ ገፆችን እና ቻናሎችን ባለመከተል የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ይከላከሉ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::