ዛሬ ሁሉም የሀገር ውስጥ በረራዎች ተሰርዘዋል? 

በዛሬው እለት ሁሉም የሀገር ውስጥ በረራዎች እንደተሰረዙ የሚገልፁ ፅሁፎች ማህበራዊ ሚድያ ላይ፣ በተለይ ትዊተር ላይ እየታዩ ነው። ይህንን እንድናጣራ ጥያቄዎች ቀርበውልናል። 

ኢትዮጵያ ቼክ ይህን መረጃ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አጣርቷል። 

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘነው መረጃ እንደሚጠቁመው ለበረራ በሰአቱ ሊደርሱ የማይችሉ መንገደኞች ሊኖሩ ይችላሉ፣ እንዲሁም ብዙ መንገደኞች የሌሉባቸውን በረራዎች ወደሚቀጥለው በረራ ማሸጋሸግ ሊኖር ይችላል። 

“ይህ በየቀኑ ያለ ስራ ነው። ከዛ ውጪ ምንም የተለየ ነገር የለም፣ በረራዎች አሉ፣ መንገደኞችም እየተስተናገዱ ነው። ለምሳሌ ዛሬ ጠዋት ወደ ጅግጅጋ ሁለት በረራዎች ተከናውነዋል” የሚል መልስ አግኝተናል። 

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ዳይሬክተር ጀነራል ኮ/ል ወሰንየለህ ሁነኛው በበኩላቸው “በረራዎች እንደበፊቱ እንደቀጠሉ ናቸው። ከሌላው ቀን ምንም የተለየ ነገር የለም” ብለው ለኢትዮጵያ ቼክ ምላሽ ሰጥተዋል። 

በሌላ በኩል ዛሬ ወደ ባህርዳር፣ ደሴ እና ሌሎች ከተሞች በረራዎች እንዳሉ ኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጧል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::