አሶሴትድ ፕረስ የኢትዮጵያ ምርጫ በድጋሜ እንዲራዘም በመደረጉ ዙሪያ ምን አለ?

አሶሴትድ ፕረስ የኢትዮጵያ ምርጫ በድጋሜ እንዲራዘም የተደረገው የተወሰኑ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫው አንሳተፍም ካሉ በሁዋላ እንዲሁም በትግራይ ክልል ባለው ግጭት ምክያት ክልሉ ላይ ምርጫ ስለማይካሄድ ነው የሚል ዘገባ አስነብቧል። 

ይሁንና የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የድምፅ መስጫ ቀን ማራዘም ያስፈለገበትን ምክያት በትናንትናው እለት ግልፅ ያረገ ሲሆን ምክንያቶቹንም አስቀምጧል። 

በቦርዱ የቀረቡት ምክንያቶች: 

– የድምፅ መስጫ ወረቀት ህትመት የወሰደው ጊዜ በመኖሩ 

– የመራጮች ምዝገባ የወሰደው ተጨማሪ ጊዜ በመኖሩ 

– ለቁሳቁስ ማጓጓዣ በቂ ጊዜ ስለሚያስፈልግ 

  በአንድ ምርጫ ጣቢያ ሶስት የነበሩትን የምርጫ አስፈፃሚዎች መጨመር ስለሚያስፈልግ እንደሆነ አል አይን ዘግቧል። 

ስለዚህ በአሶሴትድ ፕረስ ምክንያት ተብሎ የቀረበው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን መገንዘብ ይቻላል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::