ለጥያቄዎቻችሁ መልስ!

ይህ “US ARMY BASE CAMP Job in Gulf” የሚል የፌስቡክ ገፅ በርካታ የስራ እድሎችን እያስተዋወቀ ይገኛል፣ አንድ የኢትዮጵያ ቼክ ተከታታይም እንድናጣራለት ጥያቄ አቅርቧል።

ይህ ገፅ ከሶስት ሺህ በላይ ተከታይ ያለው ሲሆን ሹፌሮች፣ ምግብ አብሳዮች፣ ጥበቃዎች እና ሌሎች የስራ እድሎች እንዳሉ ይጠቅሳል፣ መረጃው ለብዙ ሰዎች እንዲደርስም ለፌስቡክ ክፍያ በመፈፀም በ sponsored መልኩ ያሰራጫል።

ገፁ የተከፈተው የዛሬ አራት አመት ግድም ከኔፓል ሀገር ውስጥ እንደሆነ መለየት የሚቻል ሲሆን ምንም አይነት ከአሜሪካ መንግስት ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚያረጋግጥ መረጃ ግን የለውም። በርካታ አሳሳች እና አጭበርባሪ ገፆች እንደሚያደርጉት ድረ-ገፅም ሆነ ሌሎች የስልክ አድራሻዎች የሉትም። ገፁ ከአመት በፊት ይጠቀምበት የነበረውን የኔፓል ቋንቋ (ኔፓሊ) በመተው አሁን ላይ በእንግሊዘኛ መረጃዎችን እየለቀቀ ይገኛል።

ገፁ የሚያወጣቸው ማስታወቂያዎች ስር በርካታ ኢትዮጵያውያን “እንዴት ማመልከት እንችላለን?” የሚል መልእክቶችን ሲያስቀምጡ ተመልክተናል።

እንዲህ አይነት ማጭበርበርያዎች እየተለመዱ እየመጡ ስለሆነ ፌስቡክ ማረጋገጫ ከሰጣቸው ገፆች እና ትክክለኛ ድረ-ገፆች ውጪ ያሉ ማመልከቻዎችን ባለመቀበል ራስዎን ከመታለል ያድኑ ለማለት እንወዳለን።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::