የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት እድሳት ወጪ ጉዳይ!

ትላንት የተመረቀዉ የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት እድሳት ወጪን በተመለከተ የተለያዩ ሚዲያዎች የተለያዩ የገንዘብ መጠን በመጥቀስ እየዘገቡ ይገኛሉ።

ለምሳሌ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ለማዘጋጃ ቤቱ እድሳት ከ2.2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉን በፌስቡክ ግጹ ዘግቧል። የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ደግሞ እድሳቱ ከ1.5 ቢሊዮን ብር በላይ መፍጀቱን አስነብቧል።

ይሁን እንጂ ሁለቱም ሚዲያዎች የቁጥሮቹን ምንጭ አልጠቀሱም።

የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮም በትላንትናዉ እለት ፕሮጀክቱ ከ1.5 ቢልዮን ብር በላይ ወጪ እንደተደረገበት በፌስቡክ ገጹ ከጻፈ ከሁለት ሰዓታት በዃላ ቁጥሩን ወደ 2.2 ቢልዮን ብር ቀይሯል።

እነዚህ ለአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት እድሳት ወጡ የተባሉት ሁለት የተለያዩ ቁጥሮች በማህበራዊ ትስስር ገጾች ተጠቃሚዎች ዘንድ ብዥታን ሲፈጥሩም ተመልክተናል።

ኢትዮጵያ ቼክም ጉዳዩን በተመለከተ ባደረገዉ ማጣራት የአዲስ አበባ የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽህፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ደቦ ቱንካ (ኢንጂነር) ለማዘጋጃ ቤቱ እድሳት ከ2.2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉን በምርቃት ስነ-ስረዓቱ ላይ መናገራቸዉን ኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጧል።

ከ57 ዓምታት በላይ ያስቆጠረዉ የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት የህፃናት መዋያ፣ ፤ቤተ-መጽሀፍት ፣ የስልጠናና የምርምር ክፍሎች፣ ክሊኒክ፣ የቴአትር አዳራሽ፣ የሰራተኞች እና የባለጉዳዮች መመገቢያ አዳራሽና ሌሎች አገልግሎቶችን በዉስጡ የያዘ እንደሆነ ተነግሯል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::