በትናንትናው እለት ስማቸውን ቀይረው የነበሩ የትዊተር አካውንቶች!

የትዊተር አካውንቶችን ስም በቀላሉ መቀያየር ይቻላል፣ ይህም ለሀሰተኛ መረጃዎች ስርጭት እገዛ እያረገ ይገኛል።ፌስቡክ ላይ ስም መቀያየር ቢቻልም ድርጅቱ ጥናት አድርጎ መጀመርያው ከነበረው ስም ጋር በጣም የተለየ ከሆነእና ለስም ለውጡ ምክንያት ካልቀረበ አይቀበልም።

በትናንትናው እለት ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ማለፏን ተከትሎ የትዊተር ስማቸውን ቀይረው ትዊትሲያረጉ የነበሩ አካውንቶችን ተመልክተናል።

አንዱ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ስም እና ምስል የተከፈተ እና 2 ሺህ በላይ ተከታይ ያለው የትዊተርአካውንት ሲሆን ከእግር ኳስ ጋር የተያያዙ በርካታ መረጃዎችን ካጋራ በሗላ እና በርካታ ሰዎችም መረጃውንካሰራጩለት በሗላ ስሙን መልሶ ወደቀድሞው መልሶታል።

ሌላኛው አካውንት ደግሞ ስሙን ወደ ኒጀር ፕሬዝደንት መሀማዱ ኢሶፉ ትናንት የቀየረ ሲሆን ይህም በተመሳሳይከእግር ኳስ ጨዋታው ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ካጋራ በሗላ መልሶ ስሙን ቀይሯል።

ምናልባትም ብዙዎች ልብ ያላሉት እና እኛም እንድናጣራለቸው የጠየቁን ሰዎች እንደሚያመለክተው የጠ/ሚርአብይም ሆነ የፕሬዝደንት ኢሶፉ ትክክለኛ አካውንቶች በትዊተር የማረጋገጫ ምልክት ያላቸው መሆናቸውንነው።

ማህበራዊ ሚድያ ላይ በዚህ መልኩ ለቀልድ ወይም ሰዎችን ለማስደሰት ታስቦ የአካውንቶችን ስም በመቀያየርየሚሰራጭ መረጃ በራሱ ጉዳት ባይኖረውም በተመሳሳይ መልኩ ለሀሰተኛ መረጃ መሰራጨት በር ከፋች ነው።

ተመሳስለው የተከፈቱ ሀሰተኛ ገጾችን እና አካውንቶችን ባለመከተል ከሀሰተኛና ከተዛቡ መረጃዎችን ስርጭትእራስዎን ይጠብቁ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::