ሁለት የፌስቡክ ማረጋገጫ (verification) ያላቸው የትምህርት ሚኒስቴር ገፆች ጉዳይ!

አንዳንድ የኢትዮጵያ ቼክ ተከታታዮች ሁለት የፌስቡክ ማረጋገጫ ያላቸው የፌስቡክ ገፆች እንዳሉ ጠቁመውን ምክንያቱ ምን እንደሆነ እንድናጣራ ጥያቄ አቅርበውልናል።

ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ ትምህርት ሚኒስቴርን ያናገረ ሲሆን 214,000 ተከታይ ያለው ገፅ ከዚህ ቀደም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር (MoSHE) ይጠቀምበት እንደነበር ተገልጿል።

“ፌስቡክን በማናገር የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ገፅ ላይ ያሉትን ተከታዮች ወደ ዋናው ገፅ (364,000 ተከታይ ወዳለው) ለመውሰድ እየሞከርን ነው” የሚል መልስ ያገኘን ሲሆን ይህን ማድረግ እስካሁን እንዳልተሳካ ተገልጿል።

“በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ሁኔታውን አይተን ካልተሳካ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የነበረው ገፅ እንዲሰረዝ እናደርጋለን” ብሏል ሚኒስቴሩ።

የቀድሞው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ሚኒስቴር ስር እንዲጠቃለል መደረጉ ይታወሳል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::