የአባይ ግድብ ወይስ የናይል ግድብ?

አንድ ካርታን ብንመለከት ወይም የጂኦግራፊ ትምህርታችንን ብናስታውስ ከታች ሀገራት የሚፈሰው ኋይት ናይል እና ከኢትዮጵያ የሚፈሰው ብሉ ናይል (ወይም አባይ) ካርቱም ላይ ከተገናኙ በኋላ ስሙ የናይል ወንዝ እንደሚሆን እንረዳለን።

ነገር ግን ዛሬን ጨምሮ ከሰሞኑ በርካታ አለም አቀፍ ሚድያዎች የህዳሴ ግድብን “የናይል ግድብ” የሚል ስም እንደሰጡት ኢትዮጵያ ቼክ ተመልክቷል፣ ይህም ማለት ግድቡ የተሰራው ከኢትዮጵያ ውጪ በሚገኘው የናይል ወንዝ ላይ እንደሆነ ያመላክታል። አልጀዚራ እና ኤፒ “የብሉ ናይል ግድብ” የሚል የተሻለ ትርጓሜ ተጠቅመዋል።

ይህ ነገር ሲደጋገም እውነት የመሰለ፣ በርካቶችም እንደ እውነት የተቀበሉት ውሸት እየሆነ እንደመጣ ታዝበናል። ከዚህም በተጨማሪ አንዳንድ የመንግስት ሚድያዎች “የናይል ግድብ” የሚሉ ዜናዎችን እያጋሩ እንደሆነ ተመልክተናል።

ሲሆን ሲሆን ግድቡን በትክክለኛ ስሙ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ብሎ መጥራት፣ ካልሆነም በአባይ ወይም በብሉ ናይል ግድብነቱ መጥራት ትክክለኛው አካሄድ ነው።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::