ይህ ፎቶ የቀድሞው የሱዳን መከላከያ ሚኒስቴር ኮ/ል ኢብራሂም ሸምሰዲን ነው?

ከ1.1 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሉት እንደወረደ (Endewerede) የተባለ ይህ የፌስቡክ ገጽ የቀድሞው የሱዳን መከላከያ ሚኒስትር ኮ/ል ኢብራሂም ሸምሰዲንን ያሳያሉ ያላቸውን ምስሎች ዛሬ አጋርቷል። ከፎቶዎቹ ጋር ተያይዞ የቀረበው ጹሁፍ እ.አ.አ በ2001 በአውሮፕላን አደጋ እንደሞቱ የሚነገርላቸው ኮ/ል ኢብራሂም በቀድሞው የሱዳን ፕሬዝደንት ኡመር አልበሽር ትዕዛዝ ከመሬት በታች በሆነ ድብቅ እስር ቤት ሲማቅቁ እንደነበሩ ያትታል።

ኢትዮጵያ ቼክ በሪቨርስ ኤሜጅ ባደረገው ማጣራት ፎቶዎቹ የኮ/ል ኢብራሂም አለመሆናቸውን አረጋግጧል። በፎቶዎቹ ላይ የሚታየው በርሀብ የተጎዳው ግለሰብ ኬኒያዊ ሲሆን ፎቶዎቹ የተነሱት አምና በሰሜን ኬኒያ እና በስምጥ ሸለቆ አካባቢዎች በድርቅ ምክንያት ርሃብ በተከሰተበት ወቅት ነበር።

ፎቶዎቹን ለመጀመሪያ ጊዜ በመጋቢት ወር 2019 ዓ.ም በትዊተር ገጹ ያጋራው የቢቢሲ ጋዜጠኛ የሆነው ሮንክሊፍ ኦዲት ነበር።

ተንቀሳቃሽ ምስሉን በዚህ ሊንክ አማካኝነት ማየት ይቻላል: https://twitter.com/RoncliffeOdit/status/1108566831219048449

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::