የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲን ስምና አርማ በመጠቀም የተከፈቱ የፌስቡክ ገጾች መኖራቸውን ተመልክተናል!

ከገጾቹ መካከል ይህ “Oda Bultum University- ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ” የሚል ስያሜ የሚጠቀምና ከ11,340 በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጽ ይገኝበታል።

ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ከላይ የተገለጸው የፌስቡክ ገጽ ሀሠተኛ መሆኑን ለኢትዮጵያ ቼክ አስታውቋል። በገጹ የሚተላለፉ መልዕክቶችም ዩኒቨርሲቲውን እንደማይወክሉ ገልጿል።

ትክክለኛው የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የፌስቡክ ገጽ ከ14,530 በላይ ተከታዮች ያሉት ሲሆን ይህን ማስፈንጠሪያ በመከተል ማግኘት ይቻላል: https://www.facebook.com/OBUEthiopia

ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ አካውንቶችንና ገጾችን ብቻ በመከተል እራስዎን ከተዛቡ እና ሀሠተኛ ከሆኑ መረጃዎች ያርቁ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::