በአንድ የሩጫ ውድድር ወቅት አትሌት ሀይሌ ገ/ስላሴን የመታው ኬንያዊ አትሌት ፖል ቴርጋት አይደለም! 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት ዛሬ ከኬንያው አትሌት ፖል ቴርጋት ጋር ያደረገውን ቃለመጠይቅ ይዞ ወጥቷል። በዚህ ዜና ላይ “በረዥም ርቀት ውድድር የሀይሌ ተፎካካሪ ከነበሩ ስመ ገናና አትሌቶች መካከል የሚጠቀሰው አትሌት ፖል ቴርጋት ሀይሌን በውድድር ማሸነፍ ሲያቅተው ጀርባውን በቡጢ የመታበትን አጋጣሚ ብዙዎች አይረሱትም” የሚል ሀተታ አቅርቧል። 

ኢትዮጵያ ቼክ በዚህ ዙርያ የወጡ በርካታ ዜናዎችን የተመለከተ ሲሆን እ.አ.አ በ1992 በሴኡል፣ ደቡብ ኮርያ በተደረገ የአለም የወጣቶች ሻምፒዮና ላይ የአትሌት ሀይሌ ገ/ስላሴን ጀርባ የውድድሩ መጨረሻ ላይ የመታው አትሌት ጆስፋት ማቹካ እንጂ አትሌት ፖል ቴርጋት እንዳልሆነ ማየት እንችላለን። 

አትሌት ማቹካ በዚህ ድርጊቱ የብር ሜዳልያውን የተነጠቀ ሲሆን ሌሎች ቅጣቶችንም አስተናግዶ ነበር። ከዛ ወዲህ ግን በድርጊቱ እንደተፀፀተ እና በግሉ አትሌት ሀይሌን ይቅርታ እንደጠየቀ ገልፆ ነበር። 

ቪድዮውን ለማየት: https://youtu.be/RbxfKavcCdA

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::