ሀሰተኛ የትዊተር አካውንት ማሳወቂያ!

ይህ 3,400 በላይ ተከታዮች ያሉት እና በኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍኃላፊ በአቶ ታዬ ደንደአ ስም እና ምስል የተከፈተ የትዊተር አካውንት የእርሳቸው አለመሆኑን አቶ ታዬለኢትዮጵያ ቼክ እንዳሳወቁ በቅርቡ መረጃ አቅርበን ነበር።

ይሁንና አሁንም በርካታ ሰዎች እዚህ ተመሳስሎ የተከፈተ ገፅ ላይ የሚገኙ ፅሁፎችን እያጋሩ እንደሆነተመልክተናል።

የአቶ ታዬ ትክክለኛ የትዊተር አካውንት 3,100 በላይ ተከታዮች አሉት። ትክክለኛውን አካውንት ለማግኘት ይህንሊንክ በመከተል ማግኘት ይቻላል:- https://twitter.com/DendeaTaye?s=09

ተመሳስለው የተከፈቱ ገፆችን፣ አካውንቶችን እንዲሁም ቻናሎችን ባለመከተል የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትንለመከላከል አስተዋፅኦ ያድርጉ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::