ትክክለኛው ምስል የትኛው ነው? 

ዛሬ ጠዋት ፎቶፎረንሲክ በመጠቀም በምስሉ ላይ የሚታየውን ፎቶ በተመለከተ አንድ መረጃ አቅርበን ነበር። ይህን ተከትሎ ሁለት የቪድዮ ሊንኮች ከተከታታዮቻችን ደርሰውን እንድናጣራ ጥያቄ ቀርቦልናል።

ይህ ከቪድዮው ላይ የተወሰደው ምስል ትክክለኛ እንደሆነ እንዲሁም ፎቶፎረንሲክ ተጠቅመን ስናጣራ የውጤቱ ንባብ ላይ ስህተት እንደሰራን ተረድተናል። ለተፈጠረው ስህተት ከፍ ያለ ይቅርታ እየጠየቅን ፎቶው ትክክለኛ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን፣ አጋርተነው የነበረው መረጃንም አንስተነዋል።

ዘገባ በመስራትም ሆነ መረጃ በማጣራት ሂደት ስህተቶች አንዳንድ ግዜ ያጋጥማሉ፣ ስህተት ከተሰራ ደግሞ ተከታትለን ማረም ግዴታችን እና ሀላፊነታችን ስለሆነ ይህን ለማድረግ ሁሌም ዝግጁ መሆናችንን በዚህ አጋጣሚ ለመግለፅ እንወዳለን።

ኢትዮጵያ ቼክ።

Photo: taken from a video screenshot.

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::