እነዚህ ፎቶዎች ከአራት ወር በፊት የተነሱ ናቸው?

“Daily Mercato” የተባለና ከ448 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ ገጽ “ሰበር ዜና” በሚል ርዕስ ስር EBC እና FANA ባህርዳር ላይ መከላከያን ለመቀላቀል የመጡ ወጣቶች ብለው የለጠፋት ምስል ከ4 ወር በፊት የስራ ማስታወቂያ ተለጥፎ ለመመዝገብ የመጡ ወጣቶች ምስል ነው” የሚል ጽሁፍ አጋርቷል። ከጽሁፉ ጋርም አምስት ፎቶዎች ለጥፏል። ይህ ጽሁፍም በበርካታ ሰዎች ሲጋራ ተመልክተናል።

ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት ከላይ የተጠቀሰው ገጽ ያጋራው መልዕክት ሀሠተኛ መሆኑን አረጋግጧል። የተጋሩት ፎቶዎች ዛሬ በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ነዋሪ የሆኑ ወጣቶች የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለመቀላቀል ተሰብስበው የሚያሳዩ ናቸው።

ፎቶዎቹ የተነሱት በባህርዳር ከተማ በሚገኘው ሙሉዓለም የባህል ማዕከል አዳራሽና ግቢ ውስጥ ሲሆን በከተማው ኮሚኒኬሽንና በአማራ ኮሚኬሽን የፌስቡክ ገጾች እንዲሁም በከተማው ነዋሪ በሆኑ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች በፎቶና በቪዲዮ መልክ የተጋሩ ናቸው።

ኢትዮጵያ ቼክ ከዚህ ቀደምም በዚህ ገጽ የተሰራጨ ሀሠተኛ መረጃ ማጋለጡ ይታወቃል።

በአንጻራዊነት ታማኝ የሆኑ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችንና አካውንቶችን በመከተል እራስዎን ከሀሠተኛና የተዛባ መረጃ ይጠብቁ፤ ትክክለኛነታቸው ያልተረጋገጠ ጽሁፎችንና ምስሎችን አያጋሩ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::