በዚህ ምስል ዙርያ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ለኢትዮጵያ ቼክ ቀርበዋል! 

ሰሞኑን ዩኒሴፍ እንዲሁም ሌሎች አለም አቀፍ የበጎ አድራጊ ድርጅቶች ባወጡት እጅግ አሳሳቢ መግለጫ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በትግራይ ክልል ውስጥ በረሀብ መሳይ ሁኔታ (famine like conditions) ውስጥ እንደሚገኙ ይፋ አድርጓል። ዩኒሴፍ ከዚህ ጋር አያይዞም 33 ሺህ ህፃናት በዚሁ የከፋ ረሀብ ምክንያት አስቸኳይ ድጋፍ ካላገኙ የሞት አደጋ እንደተጋረጠባቸው አስነብቧል። 

ከዚህ ጋር ተያይዞ ይህን አሳዛኝ ምስል ይዘው ማሕበራዊ ሚዲያ ላይ በሁለት ጎራ የተከፈሉ ግለሰቦች ሲያጋሩት እና አንዱ ሌላውን ሲከስ አስተውለናል። አንዳንዱ በዚህ አመት በትግራይ ክልል የተነሳ ፎቶ እንደሆነ ሲገልፅ ሌላው ደግሞ እ.አ.አ በ2016 የተወሰደ የቆየ ምስል እንደሆነ ሲያስረዳ ተስተውሏል። 

ኢትዮጵያ ቼክ በምስሉ ላይ ማጣራት አድርጓል። በዚህም መሰረት እውነታው ምስሉ ዘንድሮም ይሁን በ2016 ሳይሆን በ1984 በኢትዮጵያ በተከሰተው ረሀብ ወቅት የተነሳ ፎቶ ነው። 

ፎቶውን ያነሳው ጆን አይዛክ የተባለ የፎቶ ባለሙያ ሲሆን በወቅቱ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያነሳው ፎቶ እንደሆነ አረጋግጠናል። ግለሰቧ በርሀብ ምክንያት ክፉኛ ተጎድታ ህክምና ለመከታተል ወደ መቐለ ከተማ እንደመጣችም የፎቶው መግለጫ ያሳያል። 

ተጨማሪ የፎቶው ዝርዝር ይህን ይመስላል: 

Unique Identifier: UN7779870  

NICA ID: 36547  

Production Date: 11/11/1984 4:34:33 PM  

Country: Ethiopia 

Credit: UN Photo/John Isaac 

File size: 1MB  

በቀጥታ የተመድ ድረ-ገፅ ላይ ለማየት: https://dam.media.un.org/CS.aspx?VP3=DamView&VBID=2AM94S5V09QG&SMLS=1&RW=1391&RH=814

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::