ይህ በአፋር ክልል ተጠልለው የሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ላይ ድብደባ መፈጸሙን ያሳያል ተብሎ የቀረበ ምስል የተሳሳተ ነው! 

‘Afar Fedralist Diaspora Coordination Committee’ የሚል ስያሜ ያለውና ከ1,200 በላይ ተከታዮች ያሉት የትዊተር አካውንት በአፋር ክልል ዞን ሁለት ተጠልለው የሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ላይ ድብደባ መፈጸሙን እንዲሁም በግዴታ ወደሌላ ቦታ መዛወራቸውን የሚገልጽ መልዕክት ከሰዐታት በፊት አጋርቷል። አካውንቱ ከመልዕክቱ ጋር ፎቶዎችን አያይዟል። 

ኢትዮጵያ ቼክ የሪቨርስ ኢሜጅ ሰርች መተግበሪያዎችን በመጠቀም ባደረገው ማጣራት ከላይ የተጠቀሰው አካውንት ካጋራቸው ፎቶዎች መካከል አንዱ ከሁለት ቀናት በፊት በጅቡቲ የተነሳ መሆኑን አረጋግጧል። 

ይህ አይኑ አካባቢ ጉዳት የደረሰበትን ግለሰብ የሚያሳየው ፎቶ ከሁለት ቀናት በፊት በጅቡቲ በተፈጠረ ግጭት ወቅት የተነሳ ሲሆን ፈረንሳይኛና አፋርኛ ተናጋሪ በሆኑ የአፍሪካ ቀንድ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በስፋት ሲጋራ ነበር። 

አሳሳች፣ ከአውድ ውጭ የሚቀርቡ እና የተነካኩ ምስሎችን ባለማጋራት ለሀሰተኛ መረጃ ስርጭት መቀነስ የበኩላችንን አስተዋጽኦ እናበርክት።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::