በፎቶው ላይ የሚታዩት የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክርቤት አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም ናቸው?

ከ28 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት ‘ወሎ-Wollo News’ የተባለ የፌስቡክ ገጽን ጨምሮ በርከት ያሉ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በፎቶው ላይ ከጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እና ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ ጋር የተቀመጡት ግለሰብ የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክርቤት አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም መሆናቸውን የሚገልጹ መረጃዎች ለጥፈዋል።

ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት በፎቶው ላይ ደብዛዛ አረንዴ ቀሚስ ለብሰው የሚታዩት ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም አለመሆናቸው አረጋግጧል።

በወቅቱ በስፍራው የነበሩ የጤና ጥበቃ የስራ ባልደረቦች ለኢትዮጵያ ቼክ እንደገለጹት በፎቶው ላይ የሚታዩት የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ወይሰሮ ሳህረላ አብዱላሂ ናቸው። ፎቶው የተወሰደው ባሳለፍነው ቅዳሜ በመቀሌ ከተማ በተከናወነ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ማስጀመሪያ መርሐግብር ወቅት ነበር።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ችሎት መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም ባስዋለው ችሎት ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም በዋስ እንዲለቀቁ እንዲሁም ቀዳሚ ምርመራ እስከሚሰማ ድረስ በሰርቪስ ማረፊያ እንዲቆዩ መወሰኑ ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::