በመከላከያ ሠራዊት ወታደራዊ ተሽከርካሪ ላይ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አርማዎች ተሰቅለው የሚታይበት ፎቶ ትክክለኛ ነው?

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ንብረት የሆነ ኡራል ወታደራዊ ተሽከርካሪ ላይ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር አርማዎች ተሰቅለው የሚታይበት ፎቶ ዛሬ በማህበራዊ ትስስር ገጾች በስፋት ሲዘዋወር ኢትዮጵያ ቼክ ተመልክቷል።

ይህ ፎቶ በተደጋጋሚ ከተጋራባቸው የማህበራዊ ትስስር ገጾች አንዱ ‘Abebe Belew Group’ የተባለና ከ75 ሺህ በላይ አባላት ያሉት የፌስቡክ ቡድን ይገኝበታል።

በዚህ ቡድን ፎቶውን ካጋሩት መካከል አንዱ የሆነው ዋርካው ጎንደር “ሸዋ ላይ የታወጀው ጦርነት በመንግስት የሚደገፍ ስለመሆኑ ከዚህ በላይ ማረጋገጫ የለም!….በመከላከያ መኪና (ኦራል) ላይ ባንዴራውን እያውለበለበ ያለው ኦነግ ሸኔ (“የኦሮሚያ ልዩ ሀይል”) ነው። ይህ በኦሮምያ ክልል መንግስት፣ በኦነግ ሸኔና በመከላከያ መካከል ልዩነት እንደሌለ ያሳየናል” የሚል ጽሁፍ አስፍሯል።

ኢትዮጵያ ቼክ የፎቶ ፎረንሲክ መገልገያ መሳሪዎችን በመጠቀም ባደረገው ማጣራት ፎቶው የተጨቆነ (photoshopped) መሆኑን አረጋግጧል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ ቼክ የሪቨርስ ኢሜጅ መፈለጊያ መተግበሪያዎችን በመጠቀም ባደረገው ማጣራት በትክክለኛው ወይንም ባልተጨቆነው ፎቶ የኢፌድሪ ሠንደቅ አላማ የሚታይ መሆኑን አረጋግጧል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::