ይህ ፎቶ የኤርትራ ወይም የአማራ ልዩ ሀይሎችን ያሳያል?

ለበርካታ ወራት የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ስለመገኘታቸው በመንግስት ማስተባበያ ሲሰጥ ቆይቶ በቅርቡግን በእርግጥ እንዳሉ ማረጋገጫ ተሰጥቷል፣ ወታደሮቹ መውጣት እንደጀመሩም በመንግስት ተገልጿል። ይህንተከትሎም በርካታ መረጃዎች ማህበራዊ ሚድያ ላይ እየተሰራጩ ይገኛል።

ለምሳሌ ‘Netsi Gual Tigray’ በተባለ ስም 1,100 በላይ ተከታዮች ያለው የትዊተር አካውንት የኤርትራ ወታደሮችንያሳያል ያለውን ፎቶ ለጥፏል/ለጥፋለች። በተለጠፈው ፎቶ ላይ የሚታዩት ወታደሮች አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ አርማበትክሻቸው ላይ አድርገዋል። ይህ ትዊት ከመቶ በላይ ግብረመልሶችን አግኝቷል።

በተመሳሳይ ‘Abdulbasit Yasin’ የተባለና አስራ ሁለት ሺህ ገደማ ተከታዮች ያሉት የፌስቡክ አካውንት ይህን ፎቶየአማራ ልዮ ሃይል ዛሬ ሻሸመኔ ላይ ሲራገፍከሚል ጽሁፍ ጋር አጋርቷል።

ኢትዮጵያ ቼክ ባደረገው ማጣራት በፎቶው ላይ የሚታዩትወታደሮችየኤርትራ ወይንም የአማራ ልዩ ኃይልአባላት አለመሆናቸውን አረጋግጧል። 

በፎቶው ላይ የሚታዩትወታደሮች” የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) አባላት ሲሆኑ ፎቶውየተነሳው ከሁለት ዓመት ከስድስት ወር በፊት ነበር። ኢትዮጵያ ቼክ በማጣራት ሂደቱ ተመሳሳይ ፎቶዎችንየተመለከ ሲሆን በተጨማሪም የአዴኃን ሊቀመንበር አቶ ተስፋሁን አለምነህን አነጋግሯል።

አቶ ተስፋሁን በፎቶው ላይ የሚታዩት ወታደሮች የአዴኃን አባላት መሆናቸውን ያረጋገጡ ሲሆን ከሁለት ዓመትከስድስት ወር በፊት የትጥቅ ትግል አቁመው ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ በሚመለሱበት ወቅት ሁመራ አካባቢየተነሱት መሆኑን ገልጸዋል።

አዴኃን መቀመጫቸውን ኤርትራ በማድረግ የትጥቅ ትግል ሲያደርጉ ከነበሩ ተቃዋሚ ቡድኖች አንዱ ሲሆንከሁለት ዓመት በፊት በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ ወስኖ ወደ ኢትዮጵያ መመለሱ ይታወሳል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::