ይህ ምስል ኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተ ድርጊትን ያሳያል?

“ባሽር ሀሺ ዩሱፍ” የተባለ ከ17,300 በላይ ተከታዮች ያሉት የትዊተር ተጠቃሚ ወሎ ውስጥ በአማራ የተገደሉ ንጹሃን ኦሮሞዎች ከመቀበራቸው በፊት ያሳያሉ ያላቸውን ሁለት ፎቶዎች ለጥፏል።

ምንም እንኳን ባሳለፍነው ሳምንት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እና የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር በሚገኙ አጎራባች ወረዳዎች በተከሰተ የሰላም መደፍረስ የዜጎች ህይዎት ማለፉ በአካባቢው ባለስልጣናትና በሚዲያዎች የተዘገበ ቢሆንም ባሽር ያጋራቸው ፎቶዎች ትክክለኛ አለመሆናቸውን ኢትዮጵያ ቼክ አረጋግጧል።

ኢትዮጵያ ቼክ የሪቨርስ ኢሜጅ መፈለጊያ መገልገያዎችን በመጠቀም ባደረገው ማጣራት ባሽር ያጋራቸው ፎቶዎች እ.አ.አ በዲሴምበር 2019 ዓ.ም dabangasudan.org በተባለ ድረገጽ የተለጠፉ ሲሆን ሱዳን ውስጥ በምዕራብ ዳርፉር ግዛት ኤል ጀኒና በተባለ ቦታ በማህሜድ አርብቶ አደሮችና በማሳሊት ጎሳ መካከል ከተፈጠረ ግጭት በሗላ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎችን ያሳያሉ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::