ከዚህ በታች የሚታየዉ የተከማቸ መሳርያ ምስል ከሰሞኑ በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ ሲዘዋወር ተመልክተናል!

ምስሉ በምዕራባዊ የሀገሪቱ ክፍል እንደተነሳ ተደርጎ ከአምስት ቀናት በፊት ጀምሮ ሲጋራ ሰንብቷል (https://twitter.com/war_noir/status/1415116037914300420?s=21)።

በሌላ በኩል ከሁለት ሚልዮን በላይ ተከታዮች ያሉት ‘Ethiopian DJ የኢትዮጵያ ሙዚቃ’ የተሰኘ የፌስቡክ ገፅም ከጥቂት ሰዓታት በፊት “በጠለምት ግንባር” የነበረ እንደሆነ ጠቅሶ ምስሉን አጋርቷል (https://www.facebook.com/182037128570741/posts/4206889626085451/)።

ይህ ምስል በተለያዩ አካላት የተለያዩ ቦታዎች ላይ እንደተነሳ ተደርጎ ከመቅረቡ ውጪ የምስሉ ባለቤት ወይም ምንጭ ማን እንደሆነ አልተገለፀም።

ኢትዮጵያ ቼክ በምስሉ ላይ ባደረገዉ ማጣራት ይህ ምስል ከሰሞኑ የተነሳ ሳይሆን ከወር ተኩል በፊት በፌስቡክ ላይ የተጋራ መሆኑን ማረጋገጥ ችሏል። በመሆኑም ይህ ምስል ‘Asseb Post’ በተሰኘ የፌስቡክ ገፅ ግንቦት 26, 2013 (June 03, 2021) ባጋራው ፅሁፍ ውስጥ ይገኛል (https://www.facebook.com/103027818359726/posts/199108715418302/)።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::