ይህ ምስል በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኝ አንድ ትልቅ ሆስፒታል እንዲህ እየተጠበቀ መሆኑን ያሳያል?

ከ91 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት KUSH Kingdom የተባለ የፌስቡክ ገጽ “በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኝ አንድ ትልቅ ሆስፒታል እንዲህ እየተጠበቀ ነው” ከሚል ጽሁፍ ጋር የቀድሞውን የመከላከያ ሰራዊት እና የፌደራል ፖሊስ ዩኒፎርም የለበሱ ወታደሮችንና ፖሊሶችን የሚያሳዩ ሶስት ፎቶግራፎች ለጥፏል።

በተመሳሳይ ከ37 ሺህ በላይ ተከታዮች ያሉት Ogaadenia Media የፌስቡክ ገጽ በርከት ያሉ ወታደሮች በአዲስ አበባ ከተማ መታየታቸውን ከሚገልጽ ጽሁፍ ጋር እነዚህን ፎቶዎች አጋርቷል።

ኢትዮጵያ ቼክ የምስል መፈለጊያ መተግበሪያዎችን በመጠቀም ባደረገው ማጣራት ፎቶዎቹ የቆዩ መሆናቸውን አረጋግጧል።

የመጀመርያው ፎቶ እ.አ.አ በሴፕቴምበር ወር 2020 ዓ.ም arabic.rt.com በተባለ ድረ-ገጽ የተጋራ ሲሆን ሁለተኛው ፎቶ ደግሞ ኦክቶበር 4 ቀን 2019 ዓ.ም በሮይተርስ የዜና ወኪል ፎቶ አንሺ አዲስ አበባ ውስጥ የተወሰደ ነው። ሶስተኛው ፎቶ በአፕሪል 11 ቀን 2016 ዓ.ም IPSNews ድረገጽ መለጠፉን የምስል ፈላጊ መተግበሪያዎች ያሳያሉ።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::