ዩትዩብ እና ትዊተር ይፋ ያረጓቸው አዳዲስ ማሻሻያዎች!

1. ዩትዩብ የዲስላይክ ቁልፍን (dislike button) በተመለከተ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል። በማሻሻያው መሰረት የዩትዩብ ተጠቃሚዎች የሰጡትን የዲስላይክ ብዛት ማየት የሚችለው የዩትዩብ ቻናሉ አስተዳዳሪ ወይም ባለቤት ብቻ ይሆናል። ዩትዩብ ማሻሻያውን ያደረገው የፈጠራ ስራና ሌሎችንም በዩትዩብ የሚያጋሩ ሰዎችን ሞራል ለመጠበቅ እንዲሁም የዲስላይክን ቁልፍ በመጠቀም የሚደርስባቸውን ጥቃት ለመከላከል መሆኑን አስታውቋል። ዩትዩብ ማሻሻያውን ከማድረጉ በፊት የሙከራ ጥናት ማካሄዱን የገለጸ ሲሆን የዲስላይክ ብዛት ለተጠቃሚዎች እንዳይታይ ሲደረግ ዲስላይክ የሚሰጡ ሰዎች ቁጥርም ቅናሽ ማሳየቱን ጠቁሟል።

2. ትዊተር ተጠቃሚዎቹ ሀሠተኛና የተዛቡ መልዕክቶችን በቀላሉ መለየት እንዲችሉ ያደርጋል ያለውን አሰራር ተግባር ላይ ማዋል መጀመሩን አስታውቋል። ባሳለፍነው ማክሰኞ ተግባር ላይ መዋል የጀመረው አዲሱ አሰራር ሀሠተኛና የተዛቡ መልዕክቶች ናቸው ተብለው በሚለዩ ትዊቶች ላይ የማስጠንቀቂያ ምልክት የሚያሳይ ይሆናል። የማስጠንቀቂያ ምልክቶቹ ብርቱካናማና ቀይ ቀለሞች ያላቸው ሲሆኑ “stay informed” እና “misleading” የሚሉ ቃላቶችን አካታው ይይዛሉ። አዲሱ አሰራር ቀይ ምልክትና “misleading” የሚል ቃል የሰፈረባቸውን ትዊቶች ላይክ ማድረግ፣ ማጋራት ወይንም ኮሜንት መስጠት ይከለክላል። አዲሱ አሰራር ተግባራዊ የሚደረገው በገሀዱ አለም ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ ተብለው በታሰቡ የተነካኩ ቪዲዮዎችና ፎቶዎች ላይ፣ ምርጫንና የድምጽ አሰጣጥን በተመለከቱ በተመለከቱ ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎች መልዕክቶች ላይ እና ኮቪድ-19ን በተመለከቱ ሀሠተኛና የተዛቡ መረጃዎች ላይ ይሆናል። ትዊተር አዲሱን አሰራር ተግባራዊ ከማድረጉ በፊት ከሀምሌ ወር ጀምሮ የሙከራ ጥናት ሲያካሂድ መቆየቱን ገልጿል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::