“ወልድያ ገብርኤል በእሳት እየተቃጠለ ነው የሚለው መረጃ የተዛባ ነው”— የወልድያ ከተማ ኮሚኒኬሽን 

የኮሚኒኬሽኑ መግለጫ እንዲህ ይነበባል: “ወልድያ ገብርኤል በእሳት እየተቃጠለ ነው የሚለው መረጃ የተዛባ መረጃ ነው። የእሳት አደጋ የተፈጠረበት ቦታ ከማንም ይምጣ ተራራ በስተሰሜን አቅጣጫ አባው ተራራ አካባቢ የተነሳ ቢሆንም የአካባቢው ማኅበረሰብ እና የጸጥታ አካሉ እሳቱ ቃጠሎው እንዳይስፋፋ የማድረግና የማጥፋት ስራ በመስራት ላይ ነው። 

ሆኖም ግን አደጋ የተፈጠረበትን ልዩ ቦታ እና ያለበትን ደረጃ አጣርቶ ከመጻፍ ይልቅ ወልድያ ገብርኤል በእሳት አደጋ እየተቃጠለ ነው ብለው የጻፉ የግለሰቦችን መረጃ በማየት ስልክ እየደወላችሁ በመጠየቅ ላላችሁት ሁሉ እውነታው ይኸ ሲሆን የቃጠሎው መንስኤ ምንድን ነው የሚለውን በሚመለከተው አካል ተጣርቶ እንደደረሰን የምናሳውቅ ይሆናል። 

ከዚህ መረጃ በመነሳት የወልድያ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን እየተቃጠለ አድርጎ በመወሰድ በመደናገጥ እየደወላችሁ ላላችሁ እንድትረጋጉ እና ሌሎችንም እውነታውን እንድታስረዱ እናሳስብለን።” 

ወልድያ ከተማ ኮሙኒኬሽን

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::