ነባር እና አዲስ ተማሪዎች መቼ ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ? 

ነባር እና አዲስ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡበትን እንዲሁም ትምህርት የሚጀመሩበትን ጊዜ በተመለከተ በርከት ያሉ ተማሪዎች ኢትዮጵያ ቼክ እንዲያጣራላቸው ጠይቀዋል። 

ኢትዮጵያ ቼክ ጉዳዩን ለማጣራት የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ወይዘሮ አመለወርቅ ህዝቅየልን አነጋግሯል። ሃላፊዋ ነባር ተማሪዎች እስከ ግንቦት 30/2013 ዓ.ም በየዩኒቨርስቲዎቻቸው እንደሚቆዩ ገልጸዋል። ትምህርት የሚጀምሩበትን ጊዜ በተመለከተ ወጥ የሆነ መርሐግብር እንደሚያስፈልግ የገለጹት ሃላፊዋ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ውሳኔዎችን በቅርቡ ያሳውቃል ብለዋል። 

ዘንድሮ ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ አዲስ ተማሪዎችን በተመለከት የሚገቡበትን ቀን የሚወስኑት የተመደቡባቸው ዩኒቨርስቲዎች መሆናቸውን ወይዘሮ አመለወርቅ አስታውቀዋል። ስለሆነም አዲስ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲዎች የሚያደርጉትን ጥሪ እንዲከታተሉ ሃላፊዋ መክረዋል። በተጨማሪም እንደ ባህርዳር ዩኒቨርስቲ ያሉ ተቋማት አዲስ ተማሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው እስከሚገቡ ድረስ የሚያነቧቸውን ሞጁሎች በኦላይን በማሰራጨት ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ቀጥታ በኢሜልዎ ለማግኘት ይመዝገቡ

    ያቀረቡትን የግል መረጃ በግላዊ መመሪያችን መሠረት እንጠብቃለን::